የዓለም መድኃኒት አምላካችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንባባና ልብስ ተነጥፎለት በአህያ ውርንጭላዋ ተጭኖ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት ‹‹ጥንተ ሆሣዕና›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይዘከራል፡፡ ሆሣዕና ማለት ‹‹አሁን አድን›› ማለት ነው፤ (ማሕቶተ ዘመን ገጽ ፻፷)
ስቅለተ ክርስቶስ ስቅለት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በገባው ቃል ኪዳን መሰረት እኛን ለማዳን መከራን ተቀብሎ በቀራኒዮ የተሰቀለበት ዕለት በመሆኑ እናከብረዋለን ።
ትንሳዔ (ፋሲካ ) ማለት ከሞት መነሳት ማለት ሲሆን እኛም ኦርቶዶክሳውያን የጌታን መነሳት የምናከብርበት በዓል ነው ።
ዕርገት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የምድር ላይ ስራውን ያጠናቀቀበትና ያረገበት በዓል ነው።
በዓለ ጲራቅሊጦስ ከትንሳኤ በኋላ በሃምሳኛ ቀን የምናከብረው የመንፈስ ቅዱስ በዐል ነው።
ደብረ ታቦር ወይንም ቡሄ! በመላው ሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዓቢይ (ዋና) በዓላት አንዱ ይሄ 'ደብረ ታቦር' የምትለው የቡሄ በዓል ነው።