በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ባልቲምር ሜሪላንድ የ2018 ዓ.ም (2025/2026) የዓመቱ የአገልግሎት መርሃ ግብር
| እለት | ሰዓት | መርሃ ግብር | |
| 1 | ዘወትር እሁድ | ከሌሊቱ 4፡00 AM – 12:30 PM | ጸሎተ ቅዳሴ፣ ትምህርተ ወንጌል፣ የሰ/ት/ቤት የመዝሙር አገልግሎት በህጻናት እና በወጣቶች፤ |
| 2 | ዘወትር ከሰኞ – ቅዳሜ | ጧት 6፡00 AM – 8፡00 AM | ጸሎተ ኪዳን |
| 3 | ዘወትር ረቡዕ | ከምሽቱ 7፡00 PM – 8፡30 PM | ጸሎትና ትምህርት |
| 4 | በየወሩ የቅድስት ሥላሴ እና የቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል | ከሌሊቱ 1፡00 AM – 12:30 PM | ጸሎተ ኪዳን ፣ ጸሎተ ቅዳሴ፣ ትምህርተ ወንጌል፣ የሰ/ት/ቤት የመዝሙር አገልግሎት በህጻናት እና በወጣቶች፤ |
ዓመታዊ በዓል
| ተ | እለት | ሰዓት | መርሃ ግብር |
| 1 | የጌታ ልደት (የገና በዓል) | በዋዜማው 2፡00 – ሌሊቱ 9፡00 ሰዓት | ማህሌትና ጸሎተ ቅዳሴ |
| 2 | የቅድስት ሥላሴ እና የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በአዘቦት ቀን ከዋለ በቀጣዩ ቅዳሜ | ከሌሊቱ 1፡00 AM – 12:30 PM | በማህሌት፣ በቅዳሴ እና በስርዓተ ንግስ |
| 3 | ሰሙነ ህማማት | ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 8፡00 ሰዓት እስከ ማታ 5፡00 ሰዓት | ጸሎት ስግደት እና ለመንፈሳዊ አገልግሎት ቤተክርስቲያኑ ክፍት ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ |
| 4 | ለፋሲካ በዓል | በዋዜማው ቅዳሜ ከምሽቱ 10፡00 ሰዓት ንጋት 3፡00 ሰዓት | በስርዓተ ማህሌት፣ በስርዓተ ቅዳሴ እና በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ይከበራል፡፡ |
- የጥምቀት በዓል እንደ አስፈላጊነቱ በአከባቢው ካሉ አቢያተ ክርስቲያናት በጋራ በመሆን ይከበራል፡፡
- የሐምሌ ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በአዘቦት ቀን ከዋለ በቀጣዩ ቅዳሜ የሚከበር ሲሆን በስርዓተ ማህሌት ቅዳሴ እና በስርዓተ ንግስ ታቦተ ህጉን ወደ ውጭ በማውጣት እንደ ሀገር ዑደት በማድረግ በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ይከበራል፡፡
- ሌሎች አባይት በዓላት እንደ አስፈላጊነታቸው በእለተ እሁድ በሚኖረን መደበኛ አገልግሎት ተደርበው ይከበራሉ፡፡