BEGIN:VCALENDAR
VERSION:2.0
PRODID:-//Baltimore Selassie - ECPv6.17.2//NONSGML v1.0//EN
CALSCALE:GREGORIAN
METHOD:PUBLISH
X-ORIGINAL-URL:https://www.baltimoreselassie.org
X-WR-CALDESC:Events for Baltimore Selassie
REFRESH-INTERVAL;VALUE=DURATION:PT1H
X-Robots-Tag:noindex
X-PUBLISHED-TTL:PT1H
BEGIN:VTIMEZONE
TZID:UTC
BEGIN:STANDARD
TZOFFSETFROM:+0000
TZOFFSETTO:+0000
TZNAME:UTC
DTSTART:20210101T000000
END:STANDARD
END:VTIMEZONE
BEGIN:VEVENT
DTSTART;VALUE=DATE:20220417
DTEND;VALUE=DATE:20220418
DTSTAMP:20260311T154519Z
CREATED:20260405T191957Z
LAST-MODIFIED:20260311T154519Z
UID:1831-1650153600-1650239999@www.baltimoreselassie.org
SUMMARY:ሆሳዕና
DESCRIPTION:አስቀድሞ በቅዱስ መጽሐፍ በነቢዩ ዘካርያስ ‹‹ለጽዮን ልጅ እነሆ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሏት›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። (ዘካ.፱፥፱) \nቅዱስ ማቴዎስ እንደጻፈው ጌታችን ኢየሱስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በቀረበ ጊዜ ሕዝቡ ተናወጠ። ሰዎች ሁሉ እርሱ በሚያልፍበት መንገድ ልብሳቸውን፣ የዘንባባ፣ የወይራና የዛፍ ቅርንጫፎች በማንጠፍ ለክብር ጌታ ምስጋናን፣ ውዳሴን አቀረቡለት። በመቅደስም ሳለ ሕፃናቱ ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሣዕና በአርያም!›› እያሉ በታላቅ ድምጽ እየጮኹ አመሰገኑት። ‹‹ሆሣዕና … ሆሣዕና… ሆሣዕና በአርያም! በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው!›› እያሉ በአናታቸው ጀርባና እቅፍ ያሉ ሕፃናትና የቢታንያ ድንጋዮች ሁሉ ሳይቀሩ በታላቅ ደስታና ሐሴት ሆነው መድኃኒት፣ አዳኝና ቤዛ ለሆነው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ ድምፅ በንጹሕ አንደበት ዘመሩለት፤ አመሰገኑት። ምድርምና ሞላዋ፣ ውቅያኖሶች፣ ባሕሮችና ተራሮች፣ ሰማይ፣ ሰማየ ሰማያት፣ ከሰማይም በላይ ያለ ሰማይ፣ የእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ በዚህ ልዩ የሕፃናት የምስጋና ጥዑም ዜማ ተሞሉ፣ በደስታም እንደ እንቦሳ ዘለሉ። \nበዚህ ልዩ ሰማያዊ ቅኔ የሰማይ ሠራዊት፡- መላእክት፣ ሊቃናት፣ አጋእዝትና መናብርት ሁሉ በአንድነት በሐሴትና በደስታ ታደሙ። በዚህ ታላቅ የምስጋና፣ የፍቅር ዜማ ምድርም በሐሴትና በደስታ ተናወጠች። የፍቅር አምላክ፣ የሰማይና የምድር ሁሉ ፈጣሪ ዝቅ ብሎ፣ የዋህና ትሑትም ሆኖ በአህያ ውርንጫ ላይ ሆኖ መጥቷልና። \nሆሣዕና ጌታችን ከዚህ ቀን በኋላ ለሚያደርገው ገቢረ ተአምራት እና የሚቀበለው መከራ የሞት ጽዋ በመሆኑ ይህ ምስጋና የጌታንን የሞት ዕለት መቅረብ የሚያበስር ዐዋጅ ነበር፡፡ በዕለተ ሆሣዕና ሕፃናት፣ የተከተሉት ሕዝቡ ሁሉ በደስታ ሲዘምሩና ሲያመሰግኑ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የሕዝበ እስራኤል በበደልና ኃጢአት ለኢየሩሳሌም ከተማ የመጥፋትና የመፍረስ ምክንያት እንደሚሆን ዐውቆና ጊዜውንም አሻግሮ አይቶ አለቀሰላት፤ ይህንንም ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ብታውቂ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሠውሯል፡፡›› (ሉቃ.፲፱፥፵፪) \nስለዚህም በዚህ ቀን አምላካችን ጌታችንና ኢየሱስ ክርስቶስ የዋህና ትሑት በመሆን ራሱን ዝቅ አድርጎ ለሰው ልጆች ሁሉ ፍቅርን እንዳሳየ እንዲሁም ሰላምን እንዳበሠረ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ ለሰው ልጆች ሰላምን የምንሻና ፍቅርን በተግባር የምንገልጽበት መልካም የምስጋናና የውዳሴ ዕለት ነው፡፡ \nሆሣዕና በአርያም!!!
URL:https://www.baltimoreselassie.org/event/%e1%88%86%e1%88%b3%e1%8b%95%e1%8a%93/
ATTACH;FMTTYPE=image/png:https://www.baltimoreselassie.org/wp-content/uploads/2022/01/hosaena.png
END:VEVENT
BEGIN:VEVENT
DTSTART;VALUE=DATE:20220422
DTEND;VALUE=DATE:20260411
DTSTAMP:20260311T154351Z
CREATED:20220113T192913Z
LAST-MODIFIED:20260311T154351Z
UID:1834-1650585600-1775865599@www.baltimoreselassie.org
SUMMARY:ስቅለት
DESCRIPTION:ስቅለተ ክርስቶስ  ስቅለት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በገባው ቃል ኪዳን መሰረት እኛን ለማዳን መከራን ተቀብሎ በቀራኒዮ የተሰቀለበት ዕለት በመሆኑ እናከብረዋለን ።
URL:https://www.baltimoreselassie.org/event/%e1%88%b5%e1%89%85%e1%88%88%e1%89%b5/
ATTACH;FMTTYPE=image/jpeg:https://www.baltimoreselassie.org/wp-content/uploads/2022/01/Christ-on-the-Cross.jpg
END:VEVENT
END:VCALENDAR