BEGIN:VCALENDAR
VERSION:2.0
PRODID:-//Baltimore Selassie - ECPv6.1.3//NONSGML v1.0//EN
CALSCALE:GREGORIAN
METHOD:PUBLISH
X-ORIGINAL-URL:https://www.baltimoreselassie.org
X-WR-CALDESC:Events for Baltimore Selassie
REFRESH-INTERVAL;VALUE=DURATION:PT1H
X-Robots-Tag:noindex
X-PUBLISHED-TTL:PT1H
BEGIN:VTIMEZONE
TZID:UTC
BEGIN:STANDARD
TZOFFSETFROM:+0000
TZOFFSETTO:+0000
TZNAME:UTC
DTSTART:20220101T000000
END:STANDARD
TZID:America/Halifax
BEGIN:DAYLIGHT
TZOFFSETFROM:-0400
TZOFFSETTO:-0300
TZNAME:ADT
DTSTART:20260308T060000
END:DAYLIGHT
BEGIN:STANDARD
TZOFFSETFROM:-0300
TZOFFSETTO:-0400
TZNAME:AST
DTSTART:20261101T050000
END:STANDARD
END:VTIMEZONE
BEGIN:VEVENT
DTSTART;VALUE=DATE:20220422
DTEND;VALUE=DATE:20260411
DTSTAMP:20260409T150309
CREATED:20220113T192913Z
LAST-MODIFIED:20260311T154351Z
UID:1834-1650585600-1775865599@www.baltimoreselassie.org
SUMMARY:ስቅለት
DESCRIPTION:ስቅለተ ክርስቶስ  ስቅለት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በገባው ቃል ኪዳን መሰረት እኛን ለማዳን መከራን ተቀብሎ በቀራኒዮ የተሰቀለበት ዕለት በመሆኑ እናከብረዋለን ።
URL:https://www.baltimoreselassie.org/event/%e1%88%b5%e1%89%85%e1%88%88%e1%89%b5/
ATTACH;FMTTYPE=image/jpeg:https://www.baltimoreselassie.org/wp-content/uploads/2022/01/Christ-on-the-Cross.jpg
END:VEVENT
BEGIN:VEVENT
DTSTART;TZID=UTC:20260411T220000
DTEND;TZID=UTC:20260412T030000
DTSTAMP:20260409T150309
CREATED:20260407T071253Z
LAST-MODIFIED:20260407T071253Z
UID:2283-1775944800-1775962800@www.baltimoreselassie.org
SUMMARY:የጌታቸንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል
DESCRIPTION:በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ፤ ባልቲሞር ሜሪላንድ። እንኳን ለጌታቸንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ። የትንሳኤን በዓል በጋራ እናክብር።
URL:https://www.baltimoreselassie.org/event/%e1%8b%a8%e1%8c%8c%e1%89%b3%e1%89%b8%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8b%b5%e1%8a%83%e1%8a%92%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8b%a8%e1%88%b1%e1%88%b5-%e1%8a%ad%e1%88%ad-2/
END:VEVENT
BEGIN:VEVENT
DTSTART;VALUE=DATE:20260412
DTEND;VALUE=DATE:20260413
DTSTAMP:20260409T150310
CREATED:20220330T103143Z
LAST-MODIFIED:20260311T154302Z
UID:1911-1775952000-1776038399@www.baltimoreselassie.org
SUMMARY:ትንሳዔ (ፋሲካ )
DESCRIPTION:“ወምድርሰ ሀለወት እራቃ ወኢታስተርኢ ወኢኮነት ድሉተ ወጽልመት መልዕልተ ቀላይ ወመንፈሰ\nእግዚአብሔር ይጼልል መልዕልተ ማይ”(ዘፍ ፩፡፪) በጥልቁ ጨለማ የነበረች ዓለም፥ ሕይወት ለማመንጨት\nየእግዚአብሔር መንፈስ በውሀው ላይ እንደንዣበበ፥ “ናሁ ይመጽእ በደመና ሰማይ ወትሬእዮ ኩሎ ዓይን”(ራዕ\n፩፡፯):: ክርስቶስም ሙታንንን ለማንሣት በሕይወት ሰጭና ሙታንን በሚቀሰቅስ ደመና አንዣቦ ይመጣል::\n“ወመጻት ደመና ብርህት ወውስተ ደመና ይነብር ወልደ እጓለ እመሕያው”(ራዕይ ፲፬፡፲፬):::: እንዲል ክርስቶስ\nየሚመጣበት ደመና አፈር ትቢያ የሆነውን የሰውን አካል ለመቀሰቅስ መለኮታዊ ኃይል አለው ይሉና፥ ከባሕርና\nከቀላይ የሚነሣው ደመና አፈር ትቢያ የሆነውን ሰርዶ የሚያለመልም፥ የነበሩበት ውኀ ሲደርቅ ወደ አፈርነት\nየተለወጡትን እንቁራሪቶች የሚቀሰቅስ ከሆነ፥ ክርስቶስ ተጭኖ የሚመጣበት ደመና አፈር ትቢያ የሆነውን ሰብአዊ\nአካል ቀስቅሶ ማስነሣት መቻሉን መጠራጠር እንደሌለብን ሊቃውንት ይናገራሉ:: \nኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አበው እነ ኤጲፋንዮስ ስለ ትንሣኤ ሲናገሩ፥ በደመና የሚንቀሳቀሱትን\nተሐዋስያንና አዝርእቶችን እንደምሳሌ ጠቅሰዋል:: “ወአንበጣሂ እምድኅረ ሞተ ይትነሣእ እምነ ምድር::\nእምልደት ዘወጽአ እምኔሁ:: ወፍሬያትሂ ይዘርዑ ወይመውቱ ቅድመ ውስተ ምድር:: ወእምድኅረ ዘመን ታወጽእ\nምድር ዘቀበረት ውስቴታ ወለእመሂ ኢሞቱ ኢየሐይው” (ሃይ ምዕ ፶፰፡፯) ብለዋል:: ይህም ማለት በወቅቱ\nየሕይወት ደመና በመሬት ላይ ሲያንዣብብ የሞተው የበሰበሰው አንበጣ ከምድር እንደሚፈላ፥ ክርስቶስ በደመና\nተጭኖ ሲመጣ አፈር ትቢያ ሆኖ እባቡ ሲልሰው የነበረው ሁሉ ሰባዊ አካል ከምድር ይነሣል::\nከክርስትና በፊት “መቃብራችሁን እከፍታለሁ:: ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ” (ሕዝ ፴፯፡፲፪)::\nእየተባለ በነብያት ሲነገር ኖሯል:: ከነብያት ወዲህ ክርስቶስ ሊወለድ አቅራቢያ “የሚሞቱ ሰዎች መነሳታቸውን\nካላመንክ ከእናት ከአባታቸው ሳይወለዱ በክረምት ከየቦታው የሚፈሉትን ፍጥረታት ተመልከት”(ሣል መቃ\n፲፡፩):: እየተባለ ስለ ሰው ልጅ ትንሣዔ በተለያዩ ምሳሌዎች ተደጋግሞ ተነግሯል:: “የስንዴም ሆነ የገብስ\nሌሎችም በምድር የሚዘሩት ሁሉ ቅንጣት ካልሞቱና ካልበሰበሱ አይበቅሉም”(ቀዳ መቃ ፰፡፳፪) እየተባለ\nተገልጿል:: ጊዜው ሲደርስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን\nትቀራለች:: ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች” (ዮሐ ፲፪፡፳፬):: እያለ የሕይወት ባለቤት ክርስቶስ ስለትንሣዔ\nመኖር አረጋገጠ:: ጊዜው ደርሶ ክርስቶስ ሞትን ድል ነሥቶ የተናገረው የመጀመሪያ ቃሉ “ተውህበ ሊተ ኩሉ\nኩነኔ ሰማይ ወምድር”(ማቴ ፳፰፡፲፰):: የሚል ነው:: ማለትም፦ በሰማይና በምድር ስልጣን በእጄ ገባ ብሎ ነው::\nቅዱስ ጳውሎስም፥ “አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም”( ፩ኛ ቆር ፲፭፡፴፮):: እያለ\nአጠንክሮና አረጋግጦ ስለትንሣዔ ያስተማረው ከዚህ ተነሥቶ ነው:: በመቀጠልም ቅዱስ ጳውሎስ “ወእምዝ ይሰአር\nደኀሪ ጸላኢ ዘውእቱ ሞት”(፩ኛ ቆሮ ፲፭፡፳፮):: እያለ አጠንክሮና አስረግጦ አስተማረ:: ማለትም፦ከእንግዲህ\nወዲህ ጠላታችን ሞት ተሽሯል:: “ዘይሔድስ ሥጋነ ትሑተ ወይሬስዮ አምሳለ ሥጋ ስብሐቲሁ በከመ\nረድኤቱ”(ፊል ፫፡፳፩):: በመሬትና በእባቡ ላይ የተሰነዘረው መርገም ተፈጸመ:: በሰው ላይ የተሰነዘረው የሩቅ\nዘመን የመቃብር ቆይታ ከወደቅንበት ለማንሣት በነበረው እቅዱ በትንሣዔው ኃይል አድሶ ያነሣን ዘንድ\nለትንሣዔያችን በኩር ሆነን:: እያለ ሰበከ:: \nክርስቶስ ስልጣን ተሰጠኝ ብሎ የተናገረውን፥ ሐዋርያት በሰፊው ካስተጋቡት አዋጅ በመንደርደር፥ የነገረ\nመለኮት እውቀት መሠረቶች ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ወበከመ ከይሲ ዘኮነ\nያመልክዎ ሰብአ ባቢሎን ሶበ ውህጠ መብልዐ ዘመጠዎ ነቢይ ተሠጥቀ እማእከሉ ከማሁ ተሰጥቀ ሞት ሶበ ውህጠ\nሥጋሁ ለእግዚእ፥ ወሶበ ውህጠ ውእተ ሥጋ ቅዱሰ ሠጠቀ ከርሶ ወተንሥአ እሙታን ሕያወ” (ሃ.አ. ፷፯፡፲፰)::\nበማለት የሰው አቅም በሚረዳላቸው በተለያዩ ምሳሌዎች እያረጋገጡ አስተማሩት:: ማለትም የባቢሎን ዘንዶ\nዳንኤል ያዘጋጀውን ሥጋ በዋጠ ጊዜ፥ እንደ ሌላው ሰው አካል የሚውጠው መስሎት፥ የጌታን ሥጋ ውጦ\nመቃብር ተሰነጠቀ ሞትም እንደ ዘንዶው ፈነዳ:: በእባብና በሰው መካከል የነበረው ዘላለማዊ የተበይና የበይነት\nግንኙነት ፈረሰ:: እባቡ በደረቱ ለዘላለም ይሳብበትና ይንከባልለበት ዘንድ ሰው ዘላለማዊ አፈር ትቢያ መሆን\nቀረለት::\nይሁን እንጅ አሁን ባለንበት ምድር በጊዜያዊ ሁኔታችን ስላለን፥ ሰይጣን በእባቡ አካል ተሰውሮ፥ አፈር\nየሆነውን አካል እንደሚልሰውና በደረቱ እንደሚሳብበት፥ በሸፍጠኞች ሰዎችም ተሰውሮ እንድንላስ እንድንበላ\nከማድረግ አይመለስምና ከዚህ አይነት ሕይወት ራሳችንን አድነን ሌላውም ከዚህ አይነት ሕይወት እንዲድን\nምስክር ለመሆን ተጠርተናል::
URL:https://www.baltimoreselassie.org/event/%e1%89%b5%e1%8a%95%e1%88%b3%e1%8b%94-%e1%8d%8b%e1%88%b2%e1%8a%ab/
ATTACH;FMTTYPE=image/png:https://www.baltimoreselassie.org/wp-content/uploads/2022/03/Tinsae.png
END:VEVENT
END:VCALENDAR