BEGIN:VCALENDAR
VERSION:2.0
PRODID:-//Baltimore Selassie - ECPv6.17.2//NONSGML v1.0//EN
CALSCALE:GREGORIAN
METHOD:PUBLISH
X-ORIGINAL-URL:https://www.baltimoreselassie.org
X-WR-CALDESC:Events for Baltimore Selassie
REFRESH-INTERVAL;VALUE=DURATION:PT1H
X-Robots-Tag:noindex
X-PUBLISHED-TTL:PT1H
BEGIN:VTIMEZONE
TZID:UTC
BEGIN:STANDARD
TZOFFSETFROM:+0000
TZOFFSETTO:+0000
TZNAME:UTC
DTSTART:20210101T000000
END:STANDARD
END:VTIMEZONE
BEGIN:VEVENT
DTSTART;VALUE=DATE:20220422
DTEND;VALUE=DATE:20260411
DTSTAMP:20260311T154351Z
CREATED:20220113T192913Z
LAST-MODIFIED:20260311T154351Z
UID:1834-1650585600-1775865599@www.baltimoreselassie.org
SUMMARY:ስቅለት
DESCRIPTION:ስቅለተ ክርስቶስ  ስቅለት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በገባው ቃል ኪዳን መሰረት እኛን ለማዳን መከራን ተቀብሎ በቀራኒዮ የተሰቀለበት ዕለት በመሆኑ እናከብረዋለን ።
URL:https://www.baltimoreselassie.org/event/%e1%88%b5%e1%89%85%e1%88%88%e1%89%b5/
ATTACH;FMTTYPE=image/jpeg:https://www.baltimoreselassie.org/wp-content/uploads/2022/01/Christ-on-the-Cross.jpg
END:VEVENT
BEGIN:VEVENT
DTSTART;VALUE=DATE:20220819
DTEND;VALUE=DATE:20220820
DTSTAMP:20220330T104148Z
CREATED:20210628T174525Z
LAST-MODIFIED:20220330T104148Z
UID:1631-1660867200-1660953599@www.baltimoreselassie.org
SUMMARY:ደብረ ታቦር
DESCRIPTION:ነሐሴ ፩፫ \nደብረ ታቦር ፣ ቡሄ ጌታ ብርሀነ መለኮቱን የገለጠበትን የምናከብርበት በዓል ነው። \nየዚህ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው። \nየማቴዎስ ወንገል ምዕራፍ ፲፯፦ ቁጥር ፩ እስከ ፭ ” ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።” \nዓቢይ መሠረቱ ይሄ ሲሆን፣ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት ‘ቡሄ’ የሚለውን ስያሜ አገኘች። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ \nበገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ፡፡ ታዲያ ያንን ማስታወሻ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የምናከብረውም ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ \nየቡሄ ዜማዎች\nበዋዜማው የሠፈር ልጆች በየቤቱ እየዞሩ ሆያ ሆዬ! አሲዮ ቤሌማ እያሉ ይጨፍራሉ። \nቁጥር 1.\nቡሄ በሉ፣ ልጆች ሁሉ\nቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ\nቅቤ ቀቡት፣ እንዳይነጣ \nክፈትልን በሩን\nየጌታዬን \nእዚያ ማዶ ነጭ ሻሽ\nእዚህ ማዶ ጥቁር ሻሽ\nየእኔማ ጌታ ነጭ ለባሽ። \nየወንዜው ነብር የወንዜው ነብር\nየኛማ ጌታ ሊሰጡን ነበር። \nሆይ ሾህዬ ሎሚታ\nልምጣ ወይ ወደማታ። \nለብሩ ነወይ ነወይ ሽጉዱ\nበአባትህ ጊዜ ሰንጋ ነው ልምዱ \nቁጥር 2\nቡሄ በሉ ! ሆ!\nቡሄ በሉ ! ሆ!\nያዳም ልጅ ሁሉ`! ሆ!\nየኛማ ጌታ ፣ የአለም ፈጣሪ\nየሰላም አምላክ፣ ትሁት መካሪ \nድምጽህን ሰማና በብሩህ ደመና\nየቡሄው ብርሃን ለኛ መጣና \nያዕቆብ ዮሃንስ ሆ! እንዲሁም ጴጥሮስ\nአምላክን አዩት ሆ! ሙሴ ኤልያስ\nአባቱም አለ ሆ! ልጄን ስሙት\nቃሌ ነውና ሆ! የወለለድኩት \nድምጽህን ሰማና በብሩህ ደመና\nየቡሄው ብርሃን ለኛ መጣና። \nቁጥር 3\nይሄ የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ በጠዋት ውርጭ የሚዘመር ሲሆን በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ ስራዬ ተብሎ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው። ሙሉ ዜማው ብዙ ቢሆንም በጥቂቱ እንዲህ ይላል \nቡሄ ና! ቡሄ\nቡሄ ና! ቡሄ\nአበባ ማለት ያደርሳል ካመት ( ጅራፍ ና ጥንጅት ድምጽ)\nኦሆ!\nቡሄ ቡሄ ና!\nቡሄ ቡሄ ና! \nቡሄ ና! ቡሄ!( የጥንጅትና የጅራፍ ድምጽ )\nቡሄ ና! ቡሄ! \nቁጥር 4\nለአባ ወራ\nመጣና መጣና ደጅ ልንጥና\nመጣና ባመቱ እንዴት ሰነበቱ፣\nክፈት በለዉ በሩን የጌታዪን\nክፈት በለዉ ተነሳ ያንን አንበሳ፣\nመጣሁኝ በዝና ተዉ ስጠኝ ምዘዝና\nየኔማ ጌታ የገደለበት\nስፍራዉ ጎድጉዶ ዉሃ ሞላበት\nእንኳን ሰዉና ወፍ አይዞርበት\nያሞራ ባልቴት ዉሃ ትቅዳበት።\nየኔማ ጌታ የሰጠኝ ካራ\nከዚህ ብመዘዉ ጎንደር አበራ፣\nየኔማ ጌታ የሰጠኝ ስንዴ\nገና ሳልበላዉ አበጠ ክንዴ።\nወይ የኔ ጌታ የሰጠኝ ሙክት\nእግንባሩ ላይ አለዉ ምልክት፣\nመስከረም ጠባ እሱን ሳነክት\nሆያ ሆዪ፣\nሆያ ሆዪ\nወይ የኔ ጌታ\nዋርካ ነህ ዋርካ\nቢጠለሉብህ የማታስነካ \nለእማ ወራ\nየኔማ እመቤት፣ እሜት እሜት\nሎሚ ተረከዝ ትርንጎ ባት\nየኔ እማ እመቤት የፈተለችዉ\nየሸረሪት ድር አስመሰለችዉ\nሸማኔ ጠፍት ማርያም ሰራችዉ\nለዝያች ለማርያም እዘኑላት\nአመት ከመንፈቅ ወሰደባት\nየኔማ እመቤት መጣንልሽ\nየቤት ባልትና ልናይልሽ።\nየኔማ እመቤት ብትሰራ ዶሮ\nሽታዉ ይጣራል ገመገም ዞሮ\nየኔማ እመቤት የጋገረችዉ\nየንብ እንጀራ አስመሰለችዉ።\n[1] \nበዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ ይሰጧቸውና እየገመጡ ጅራፋቸውን ሲያጮሁ ያመሻሉ። የቡሄ ዕለት ለእያንዳንዱ የቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ልጅ አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ በልጆቹ ልክ ይሰጣል። በቆሎ ተማሪዎች ዘንድ ደግሞ ደብረ ታቦር ‘የተማሪዎች በዓል’ ነው። ተማሪዎቹ ቀደም ብለው “ስለ ደብረ ታቦር” እያሉ እህሉንም፣ ብቅሉንም፣ ጌሾውንም ይለምኑና ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን ሁሉ ይጋብዛሉ። \nበአሁኑ ጊዜ፣ በተለይ በአዲስ አበባ ይሄንን መንፈሳዊና ባህላዊ መሠረት በመልቀቅ ለሕሙማን፣ አዛውንት እንዲሁም ለእንስሳት ድንጋጤ የሚፈጥረውንና ለእሳት አደጋ የሚያጋልጠውን ባእዳዊ ርችት በመተኮስ ሆኗል የሚከበረው። \n 
URL:https://www.baltimoreselassie.org/event/%e1%8b%b0%e1%89%a5%e1%88%a8-%e1%89%b3%e1%89%a6%e1%88%ad/
ATTACH;FMTTYPE=image/png:https://www.baltimoreselassie.org/wp-content/uploads/2021/06/debretabor.png
END:VEVENT
END:VCALENDAR